EN
Menu

About Us

የኢትዮጵያ የስኳር ህመም ማህበር

የኢትዮጵያ የስኳር ህመም ማህበር ጥር 14/1976 ተቋቁሞ፤ ከስኳር ህመም ጋር ለሚኖሩ ሰዎች የመረጃ አቅርቦት፣የህክምና እና ተያያዥ ችግሮችን ለመከላከል እንዲሁም ለማወያየት የሚያስችል መድረክ ለማዘጋጀት የተመሰረተ ማህበር ነው ፡፡ ማህበሩ የተመሰረተው ከኢትዮጵያ የህክምና ማህበር ፣ ከጤና አጠባበቅ ባለሙያዎችና ከስኳር ህመም ጋር ከሚኖሩ ሰዎች ነው ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ከህመም ጋር ተያይዞ የተመሠረተ የመጀመሪያው ማኅበርም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ስኳር ህመም ማህበር በኢ.ፌ.ድ.ሪ ሲቪል ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ መሰረት መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በአሁኑ ወቅት የማህበሩ አባላት በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ጨምሮ በ60 ቅርንጫፎች ከ20 ሺህ በላይ ደርሷል፡፡

ዓላማዎች

- የስኳር ህመም ትምህርት አቅርቦት፡- ከስኳር ህመም ጋር ለሚኖሩ ሰዎች እና የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ለህብረተሰቡ መስጠት፡፡

- ለባለድርሻ አካላት እንደ ጤና ሚኒስቴር ፣ የመንግስት ድርጅቶች እና ሌሎች የህዝብ እንዲሁም የግል ተቋማት የቴክኒክ እና የሙያዊ ምክርና ድጋፍ ማድረግ፡፡

- የስኳር ህመም እንክብካቤ አገልግሎቶችን ውጤታማ ለማድረግ እና ለማድረስ ከመንግስት ከተመደቡ የህክምና እና የጤና ክብካቤ አስተዳደሮች እና የቁጥጥር ባለሥልጣናት ጋር በመተባበር ይሠራል፡፡

- ከስኳር ህመም ጋር ለሚኖሩ ሰዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን እንዲሁም ማህበራዊ ደህንነታቸውን ማረጋገጥ፡፡

- እንደ ህትመት ፣ ስዕል ፣ ድምጽ ፣ ቪዲዮ እና ራዲዮ ጣቢያ ያሉ የተለያዩ የግንኙነት ዘዴዎችን በመጠቀም በስኳር ህመም እና በሌሎች ተያያዥ ችግሮች ላይ የትምህርት ቁሳቁሶችን ማዘጋጀት፡፡

- ከስኳር ህመም እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ጋር ተያይዞ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከል ማቋቋም፡፡

- የስኳር ህመም ጋር ለሚኖሩ ሰዎች ነፃ የህክምና እና የመድኃኒት አቅርቦት መገኘቱን የሚያረጋግጡ መንገዶችን መፈለግ፡፡

- ምርምርን ማበረታታት እና መደገፍ ፣ በዚህም የአገልግሎቶች ትክክለኛ አተገባበርን ማረጋገጥ፡፡

- ከተልእኮው መግለጫ ጋር የሚስማሙ እንደ ህዝባዊ ስብሰባዎች ፣ ሴሚናሮች ፣ አውደ ጥናቶች ፣ ኤግዚቢሽኖች ፣ ትምህርታዊ ስብሰባዎች እና ስልጠናዎች ያሉ ዝግጅቶችን ማደራጀት፡፡

- መርሃ ግብሮቹን በዘላቂነት ለመቀጠል የማህበሩን ውጤታማነት ከፍ ለማድረግ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ እና በገንዘብ ማሰባሰብ ተግባራት ውስጥ መሳተፍ፡፡

Rock a Music Category Flat Bootstrap Responsive website Template | About :: w3layouts

© 2021 EDA. All Rights Reserved | Design by BECOM IT SOLUTION PLC